ሴራሜክስ ኃላ.የተ. የግ/ማሀበር ድርጅታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተሸከርካሪዎች  ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ሴራሜክስ ኃላ.የተ. የግ/ማሀበር

ድርጅታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሴራሜክስ ኃላ.የተ. የግ/ማሀበር

ተጫራቾች

1. ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች በተናጥል ወይም ባንድ ላይ ባሉበት ሁኔታ ለመግዛት መጫረትይችላሉ፡፡

2. ለጨረታ የቀረቡትን  መኪኖች  ቀጨኔ መድሀኒያለም ቤተክረስቲያን  ከፍ በሎ  400 ሜትር ላይ በሚገኘው ኢትዮ ሴራሚክስ ቅርንጫፍ መጋዘን ግቢ ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ  የስራ ቀናት መመልከት ይችለሉ ፡፡

3. ተጫራቾች በራሳችው ወይም በህጋዊ  ወኪሎቻቸው አማካይነት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ ዋናው መስርያ ቤት የአስተዳደርና ፋይናነስ መምርያ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112 ማቅረብ ይችላሉ ፡፡

      4. ጨረታው በድርጅቱ መጋቢት 21 ቀን 2012 . ከጠዋቱ 3.00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ፡፡

5. የጨረታው አሸናፊዎች 7 የሥራ ቀናት ውሰጥ ያሸነፉበትን ተሽከርካሪ ክፈያ ፈፅመው ንብረቶችን ማንሣት አለባቸው፡፡

6. ተጫራች ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ 10 ቀናት  ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቀርቦ ካልከፈለ ለቀጣዩ አሸናፊ እድሉ ይሰጣል፡፡

7. ማንኛውም የሥም ማዘዋወረያ የጨረታው አሸናፊ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

8. ከጨረታው ቀን በፊት በመኪናዎቹ ላይ የሚከፈል ማንኛውም ክፍያ ተጫራችን ወይንም የጨረታ አሸናፊን አይመለከትም፡

9.  ጨረታው ከተመዘገቡ ተጫራቾች 3 እና 3 በላይ ከተገኙ ጨረታው ይከፈታል ፡፡

10.  ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 1000.00(አንድ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡