የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ጩኮ ወረዳ ሀሎና ጋልማ ሕብረት ሥራ ማህበር በ2013 በጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የቢሮ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት :-
- ደረጃቸው GC-6/BC-5 እናከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች በ2012 ዓ/ም ፊቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችና መሳሪያዎች በግላቸው አጓጉዘው የሚሠሩ ፤
- የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህ ተጣርቶ ኮፒ እና ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (Bank Guarantee) ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተእታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኣለታ ጩኮ ወረዳ ሀሎና ጋልማ ሕብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሻል ኦርጅናሉና ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን፣ ቴክኒካል ኦርጅናሉና ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ለየብቻቸው በስም ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አለታ ጩኮ ወረዳ ሀሎና ጋልማ ሕብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፣
- በጨረታ አከፋፈት ስነ–ሥርዓት ላይ የተነበበው ጠቅላላ ዋጋ የሂሳብ ስህተት (Arithmetic Check) ማስተካከያ በሚደረግበት ጊዜ የመጣው የሂሳብ ልዩነት (Arithmetic Error) ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ቀጥታ ከጨረታ ውድድር ወጪ ይሆናል፣
- በጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር ፐርሰንት (10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (rebate) የተደረገ ከሆነ የሥራ ተቋራጨ ቀጥታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል፣
- የግንባታ ሥራውን ለማሠራት በቅድሚያ ከተገመተው አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋ (Engineering Estimation) ከ15% /ከአሥራ አምስት በመቶ በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ ውድቅ ይሆናል፤
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፤
- አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፣
ማሳሰቢያ ፦ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ
ጩኮ ወረዳ ሀሎና ጋልማ ሕብረት ሥራ ማህበር