የሂሳብ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ሱመያ አክስዮን ማህበር ለሚጠናቀቀው በጀት ዓመት ሂሳቡን በታወቀ ኦዲተር ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሱመያ አክስዮን ማህበር ጽ/ቤት ከወረዳ 8 ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ ከሚገኘው ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ብር/አንድ መቶ ብር/ በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ ሰኔ 12 ጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 12/2012 ሱመያ አክስዮን ማህበር ጽ/ቤት በሚገኘው ሳጥን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታው ሰኔ 15/2009 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰኣት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ሀ. የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- ለ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ
- ሐ. የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና በሲፒኦ ከጠቅላላ ዋጋው 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ. የእውቅና ፈቃድ
- ሠ. አክስዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብለው ከወረዳ 08 ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0112-737373/0911-82-86-67
ሱመያ አክስዮን ማህበር