ሠላም ህጻናት መንደር
የመኪና አካል ቅጥቀጣ ሥራ ወርክሾፕ ለማሰራት
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሰላም የህጻናት መንደር በዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የመኪና አካል ቅጥቀጣ ሥራ ወርክሾፕ ለማሰራት ስለፈለገ ተገቢውን መመዘኛ የሚያሟሉ የግንባታ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ፍላጎቱ ያላችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነዱን ከዋናው መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በመግዛት ሥራውን የምትሰሩበትን ዋጋ ከተገቢ ህጋዊ ሰነዶች (ቴክኒካል ጨረታ) ጋር በተለያየ የታሸገ ፖስታ በማቅረብ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን። በዚህም መሰረት፤
- በዘርፉ ለመስራት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የ2011 ዓ.ም. ግብር የከፈሉ፤ ተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና ሌሎች ተያያዥ ህጋዊ ሰነዶችን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል፤
- ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሥራ ለመስራታቸውና፤ በቂ አቅምና ልምዱ ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ጨረታውን በታሸገ ኤንቬሎፕ እሰከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን ጨረታው ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ከጧቱ 5.00 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን በቅድሚያ እንገልጻለን። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ሰላም የህጻናት መንደር ዋና መ/ቤት አድራሻ፤ ኮተቤ ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን ጀርባ
ስልክ ቁጥር፤0116462942 አዲስ አበባ