የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሰላም አዳማ ልኳንዳ ነጋዴዎች አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የስጋ ተረፈ ምርቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ጋር ውል አስሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የስጋ ተረፈ ምርት ዓይነት |
መለኪያ |
1 |
የበሬ ቁርጥ |
በቁጥር |
2 |
ሸሆና |
በቁጥር |
3 |
የጭራ ፀጉር |
በቁጥር |
4 |
የፍየልና የበግ ቆለጥ |
ኪ.ግ |
5 |
የበሬ ቆለጥ |
ኪ.ግ |
6 |
የፍየልና የበግ ቁርጥ |
በቁጥር |
7 |
ቀንድ |
በቁጥር |
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ለዘርፉ የተሰጠውን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥና ውል ሲገባ የውል ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ተረፈ ምርት የሚያጠራቅምበት የራሱን ማቀዝቀዣ ፍሪጅ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት የራሱን የተረፈ ምርት ሰራተኛ እና ተረፈ ምርት ተረካቢ ያዘጋጃል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ቀን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሰኔ 20/2012 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅቱ ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ኣዳማ ከተማ ጎዳ ቀበሌ ጁሊዮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13
ሰልክ ቁጥር፡– 022-212-84-23
ሰሳም አዳማ ልኳንዳ ነጋዴዎች አ.ማ