ያገለገለ ዘይት እና ያገለገለ ብረት
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን በየጊዜው የሚጠራቀመውን ያገለገለ ዘይት (Lubricant) እና ያገለገለ ብረት (Metal Scrap) ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ያገለገለ ዘይት (Lubricant) በተመለከተ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ወይም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ፈቃድ ላለው እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ላለው ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ኮንትራት በመግባት ለመሸጥ ስለሚፈለግ፤ ተጫራቾች የምትገዙበትን ዋጋ በሊትር ወይም በባለ 200 ሊትር በርሜል በመግለጽ፤
- ያገለገለ ብረት (Metal Scrap) በተመለከተ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ላለው ድርጅት ለአንድ ዓመት ኮንትራት በመግባት ለመሸጥ ስለሚፈልግ፣ ተጫራቾች የምትገዙበትን ያገለገለ ብረት የጨረታ ማስከበሪያ በነጠላ ለሚጫረቱ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) ወይም በጥቅል ለሚጫረቱ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ፣ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋሲሊቲና የጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በሚኖረው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሠራተኞች ክበብ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር፡-011 4421133
የውስጥ ስልክ 212
0114401262
ፋክስ ቁጥር፡-0114420667
አድራሻ ፡– አዲስ አበባ ደብረዘይት መንገድ /ሣሪስ አካባቢ/
ፖስታ ሣጥን ቁጥር 1116
አዲስ አበባ
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ.