የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን የለስላሣ መጠጥ
- መደባለቂያ /ፍሎው ሚክስ/ ማሽን፣
- የኬሚካል ፓሌቶች፣
- ጀሪካኖች፣
- አሮጌ ጎማዎች፣
- አሮጌ ባትሪዎች እና
- የተለያዩ አገልግሎት የሰጡ ዕቃዎችን፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስራ አምስት ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ፋብሪካችን ድረስ በመምጣትና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 100.00 (ብር አንድ መቶ) ከፍለው በመግዛት መወዳደር ይችላሉ። ጨረታው በጋዜጣ ላይ መጀመሪያ ከወጣበት በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት በሠራተኞች ክበብ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቶች በጨረታው ለመሣተፍ በእያንዳንዱ ዕቃ አንፃር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬው ገንዘብ ወይም በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0116 60 48 65 74 አዲስ አበባ
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ. ሰሚት ፋብሪካ