የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር
MoMP-EGS/OT-001/2013
በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ |
የጨረታው ዓይነት |
የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
01 |
የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ |
ሰኞ ህዳር 15ቀን 2013 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 |
02 |
አልባሳት እና የተለያዩ አይነት ጫማዎች |
ሰኞ ህዳር 15ቀን 2013 ዓ/ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 |
03 |
የሚኒራሎጂ እና የጂኦ ኬሚካል ላቦራቶሪ እቃዎች |
ማከሰኞ ህዳር 16ቀን 2013 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 |
04 |
የፅዳት እቃዎች እና ሌሎች |
ማከሰኞ ህዳር 16ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 120,000.00 |
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቶች ነው፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሲሆን የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ነው፡፡
- ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 150.00 ለተራ ቁጥር 01 እና ለተራ ቁጥር 03 እንዲሁም ለተራ ቁጥር 02 እና ለተራ ቁጥር 04 100.00 በመከፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በቁጥር 7/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በአካል ቢሮው ድረስ በመምጣት ሲሆን ለሚዘገይ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በሀርድ ኮፒ ስወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ያልተካተቱ የተለያዩ የጨረታ መመሪያዎች ስላሉ ፤ ማንኛውም ተጫራች በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ ብቻ ይዞ መምጣት ይችላል፡፡
- የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እንደአስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለማብራሪያ እና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የሚያገለግል
አድራሻ ፡- ሀ/ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሴንቸሪ ሞል አጠገብ)
- ስልክ ቁጥር.. 0116 46 33 35
- ቢሮ ቁጥር 110
በማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ