የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮማያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት/ጽ/ቤት ለወረዳ ለተለያዩ መ/ቤቶች
- የሚውል አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈሉ 2013 ያደሱ።
- ተጫራቾች የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 10,000.00 ብር /አሥር ሺህ ብር/በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከአደራጃቸው ድርጅት የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከላይ በተገለጸው የጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር አንድ (1 )በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የሥራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 27/12/2012 ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ ዋናና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው በ 27/12/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30ሰዓት እስከ 8፡00 ሠዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር አንድ (1) ገቢ ማድረግ አለባቸው።ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታልተጫራቾች