የጨረታ ማስታወቂያ
ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ የሚፈልግ ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይፈልጋል፡፡
- የኦዲት ሙያ ማረጋገጫ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑ ግብር ስለመከፈሉ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ለፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲት መስሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው፣
- ተመሳሳይ ዓላማ ባለው የግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ የሥራ አፈፃፀም ያለው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው መረጃ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሚከተለው አድራሻ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አድራሻ፡- ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት ፡
- ስልክ ቁጥር፡- 0930 10 66 30 /0937 98 98 98
ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር