የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት
ከዚህ በታች የተመለከቱት ዕቃዎችን ለመግዛት፣የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና እና ሰርቪስ ለማሰራት እና የተለያዩ ግንባታዎችና ብረታ ብረቶችን ለማሰራት በወጣው ግልፅ ጨረታ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ የጨረታ አፈፃፀም መመሪያ
- ሎት ኣንድ አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት የደንብ ልብስ
- ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት አራት ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት አምስት ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎች
- ሎት ስድስት አላቂ የትምህርት እና የላብራቶሪ እቃዎች
- ሎት ሰባት የፕሪንተር፣የፎቶኮፒ ማሽን፣የማባዣ ማሽን ፣የሲስተም ዩኒት፣የጄኔሬተር እና የላፕቶፕ ኮምፒዩተር ጥገና እና ሰርቪስ
- ሎት ስምንት የተለያዩ የድንጋይና የብሎኬት ግንባታዎች፣ የተለያዩ የብረታ ብረት ስራዎች፣የአርማታ፣የሊሾና የልስን ስራዎች፣የቁፋሮ ስራዎች እና የፊኒሺንግ ስራዎች፡፡
እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታው ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ መረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች እላይ ከተራ ቁጥር 1 -8 ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ቫትን ጨምሮ የእያንዳንዱን ዕቃ ዋጋንና የጠቅላላውን ዋጋ በግልፅ ማስፈር አለባቸው፡፡
- ለጨረታው ለሚወዳደሩበት ለጠቅላላው 3000.00/ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ CPO በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ቀራኒዮ መ/ዓለም 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ
- እያንዳንዱ ተጫራች ስለሚያቀርባቸው ዕቃዎች አጭር መግለጫ ማለትም የዕቃው አምራች ድርጅት ስም፡ የተመረተበት አገር የተመረተበት ዓም መግለፅ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ የሰነዱ ገፅ ላይ በማኖር በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት ለይተው መፃፍ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከስራ ሂደቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት ዕቃዎቹን እንዲያስገባ ሲታዘዝ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 2000.00(ሁለት ሺህ ብር ብቻ) በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከስራ ሂደት ጋር ውል እንዲፈፀምና የውል ማስከበሪያውን ካስያዘ በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ የማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን እስከ 15/1/2013 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው በ18/1/2013ዓ.ም በ 400 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 4 ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ናሙናዎቹን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የመ/ቤቱ የዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ /የቴክኒክ ኮሚቴ/ የቀረቡትን የዕቃዎቹን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ጥራቱ የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ድርጅቶች/ ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው 2ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
- የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት የዕቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት ፡፡
- አልፎ አልፎ የተመለከቱት የዕቃዎች ልዩ መለያ በጠያቂ መ/ቤቶች ፍላጎት መሰረት ብቻ የዕቃውን የጥራት ደረጃ ለማመልከት የቀረበ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች ተመሳሳይና ከነዚህ የተሻሉ ዕቃዎችን ማቅረብ ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለውድድር የሚያቀርባቸውን ዕቃዎች ዓይነት ልዩ መለያ በሚለው ኮለም ውስጥ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኮፒ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል
- በመ/ቤታችን ለዕቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ቅሬታ ካለው ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቅሬታውን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል
- ማንኛውም ተጫራች ከዚህ መመሪያ ውጪ ሙስናና ከሙስና ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን ቢፈፀም ወይም በህገ ወጥ መንገድ ለማሸነፍ ቢሞከር ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል ያስያዘውም ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- በመሆኑም በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገጉትን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ሙስና ላለመፈፀም ቃል የሚገባበትን ቅፅ በተጫራቹ ተሞልቶና ተፈርሞ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል
- ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ለጥገና እና ለሰርቪስ በጨረታው አሸነፈ ሆኖ የተገለፀለት አካል ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በአምስት(5) ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
- ለጥገና በጨረታው አሸናፊው ድርጅት አስፈላጊ የሆነውን እቃ በገበያዉ ዋጋ መሰረት ማስገባትና መጠገንም ሆነ መስራት ይኖርበታል፡፡
- ጥገናውን የሚሰራው አሸናፊ ድርጅት የ1ወር ዋስትና መስጠት አለበት፡፡
- በግዥ ኣዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-8-35-08-51/54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ–ክርስቲያን ሙግቢያ(ቀራንዮ አደባባይ)
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ትምህርት መምሪያ ያቀራንዮ
መ/ዓለም 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት