የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን መተባበር እድገት አክስዮን ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚሰራ የIFRS የሂሳብ መዝገብ የድርጅቱ Asset Valuation አጫርቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም Asset Valuation ለማከናወን ህጋዊ መስፈርት ለምታሟሉና ስራውን ለማከናወን ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁ በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ ይፈልጋል፡፡
የጨረታው አላማ Asset Valuation ሲሆን ተጫራቾች ሙያውን የሚጠይቀውና ለስራ አስፈላጊ ናቸው ተብሎ የሚገመቱ በዚሁ ማስታወቂያ ያልተዘረዘሩ ተግባራትና ስራዎች ታሳቢ አድርጎ መጫረት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ድርጅታችን በአሁን ሰአት ዘጠኝ ወለል ያለው ህንፃ ያለው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ጀኔሬተር፤የቢሮ መገልገያ እቃዎች፤ሊፍት (አሳንሰር)፤ የውሃ ፓምፖች እና ሌሎችም ቋሚ ንብረቶች ያለው ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ 0922-74-53-29 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን ጨረታውን ከማስገባት በፊት ዝርዝር ስራዎች በአካል መገናኛ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት መተባባር ህንፃ ላይ ቢሮ ቁጥር 715 በመቅረብ ማረጋገጥ ይችላሉ ጨረታውን ማስገባት የሚቻለው እስከ ግንቦት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ድርጅቱ