የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የብረት ሽቦ ፤ ሚስማሮች እና ሲል ከን ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ሽያጩም ከዚህ በታች በቀረበው የጨረታ መግለጫና መመሪያ መሠረት የሚፈጸም ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድና ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000.00 ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ በሲፒኦ ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ከሚገዛበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች ግን የጨረታው ውጤት ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ተመላሽ ይሆንላቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ክፍያቸውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በድርጅቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት11/01/2013 ዓ.ም.እስከ 18/01/ ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው 19/01/ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ድርጅቱ ተስማሚ ሆኖ ካላገኘው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡-መገናኛ ስለሺ ስህን 11ኛ ፎቅ
ስልክ፡- 0116929292/93
መሰረት ተገኝ አስመጪ
MESERET TEGEGN IMPORT Tel: +251911221207
E-mail: P.O.Box 8291 Addis Ababa, Ethiopia