የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የገ/ኢ/ትብብር መምሪያ የመምሪያ መርሀቤቴ ወረዳ/ን/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት
- የብረታ ብረት ውጤቶች እና ጣውላዎች በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00(ሁለት ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል።
- እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በብር 50.00(ሃምሳ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤታችን የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመወ/ ገ/ኢ/ትብብር ዋና ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጐ በ3፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡– 011-13-20-136/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡– የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዕሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ ሰሚ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የገ/ኢ/ ትብብር መምሪያ
የመርሀቤቴ ወረዳ/ን/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት