የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር HU-HHMS-ONT-01-2013
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህይወት ፋና እስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የጽዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል።
በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ፦
- የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡
- 4.1. በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ፣
- 4.2. ማንኛውንም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፣
- 4.3. በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፣
- 4.4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፣
- 4.5.የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ፣ ሲፒኦ፣ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጽዳት ዕቃዎችን ማስረከቢያ ቦታ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና እስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የጫኝና አውራጅ ክፍያና ተያያዥ ወጪዎችን በማካተት ማቅረብ አለባቸው።
- ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሐረር ጤናና ህክምና ሳይንስ ግዥ ክፍል
ስልክ ቁጥር 0258669083/ 0256669737
ፋክስ ቁጥር 0256668081
ሐረር
አዲስ አበባ አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ አጠገብ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 15
ስልክ ቁጥር 0111571847/0915747077
አዲስ አበባ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ