የጨረታ ማስታወቂያ
ልጋ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር በአገልግሎት ምክንያት ከሥራ ውጭ የሆኑ የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሸከሪካሪዎችን እና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
- የመኪኖቹን /ንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተሸከረካሪዎቹን በሥራ ሰዓት ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ፡በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ=01 ከአየር ጤና አደባባይ ወደ ካራ ሲሄዱ ቤተሰብ ት/ቤት ጀርባ እና ካራ ቆራ ሳህሌ ብረታ ብረት ማከማቻ ባጃጅ ማዞረያ
- ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሸከርካሪዎችን /ንብረት ዝርዝር የያዘውን ፎረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 614 በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመገኘት እስከ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል::
- ተጨራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሸከርካሪ ንብረት ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድርስ ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 614 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ /ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መሰፈርት የማያሟላ ተጫራች ወደያውኑ ከጨረታ ይሰረዛል:: ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘዉን ገንዘብ ወደያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል::
- ጨረታው ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 614 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ /ንብረት መሉ ክፍያ 15% VATጨምሮ በ7 የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለማህበሩ ገቢ ሆነ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል::
- ለጨረታ በቀረቡት ተሸከረካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ የግብር ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል::
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሰጠት አይቻልም::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0115-525298 0115-526155 በሞባይል 0911235/11/0930099690 በመደወል ውይም በማህበር ዋና መ/ቤት ከግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል::