Audio Visual / Catering and Cafeteria Services / Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Foodstuff and Drinks / Music and Entertainment / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Office Machines and Computers / Others / Photography and Filming Service and Equipment / Printing and Publishing / Stationery / Transportation Service / Vehicle

ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀ/ል/ጽ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቀቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 01/2012 

ግለፅ ጨረታ ዙር 001/12 በ ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀ/ል/ጽ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት እና አስተዳደር ቡድን የግዥና  አገልግሎት ግዢ፣ የኤሌክትሮኒከስ ጥገና ግልፅ ጨረታ 

 • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 
 • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ግዥ፣ 
 • ሎት 3 ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ 
 • ሎት 4 የተለያዩ ፈርኒቸርና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፣ 
 • ሎት 5 ከ40 ሰው በላይ የሚይዝ የከተማ አውቶብስ ኪራይ በሰዓት የአገልግሎት ግዢ፣ 
 • ሎት 6 የኤሌከትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት ግዥ፣ 
 • ሎት 7 የአዳራሽና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ 
 • ሎት 8 የታሸገ ማዕድን ውሃ 0.5 ሊትር፣ 
 • ሎት 9 ልዩ ልዩ የህትመት ሥራዎች የአገልግሎት ግዥ፣ 
 • ሎት 10 ጥራቱን የጠበቀ የተዘጋጁ ቆሎ ግዥ፣  
 • ሎት 11 መድረክ ማስዋብና የዲጄ መዝናኛ ቀን ኣገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚም መሰረት ፡- በጨረታ መወዳደር ፍላጎት ያላቸው 

 • የታደሰ፤ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና በሚወዳደሩበት መስክ ከንግድ ፈቃዱ ጀርባ ገላጭ መሆን አለበት፣የግብር መክፈያ መለያ ምዝገባ፣ ተጨማሪ 15 % እሴት ታክስ ሰብሳቢ ምዝገባ፣ በኣቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ኮፒ ሠርተፍኬቶች እንዲሁም ምግብ ነክ ለሆኑት ወቅታዊ ፈቃድ እና የሚያቀርባቸው ማስረጃዎች ግልፅና ተነባቢ መሆን አለበት፡፡ በእነዚህ ኮፒ ማስረጃዎች የድርጅትዎ ማህተም ከጀርባው ይደረግበት፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ጎማ ቁጠባ ከሚገኘው የቀድሞ የልደታ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ ወይም የልደታ ፖሊስ መምሪያ ግቢ ቢሮ ቁጥር 97 ወይም 101 ከፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በመስሪያ ቤታቸን ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስት የመንግስት ግዥና አስተዳደር ቡድን ስም ሲፒኦ አሰርተው ፋይናንስ ተብሎ በተሰየመው ፖስታ ማስገባት አለባቸው ፡፡ 
 • በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት ሲጫረቱ ለሰጡት ዋጋ የጠቅላላ ዋጋ ድምር 2% በመስሪያ ቤታቸን ስም ሲፒኦ እንዲያሰሩ እያስታወስን ሎቶችን ጠቅልሎ ሲፒኦ ማሰራት ከውድድር ውጪ ስለሚያደርግዎ ሲፒኦ ሲያሰሩ ጥንቃቄ ያድርጉ 
 • ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎ ሲያስገቡ  የሚወዳደሩበትን የሎት ቁጥር መጥቀስና ፋይናንስ ከሆነ ፋናንስ፣ ቴክኒክ ከሆነ ቴክኒክ ፤ በማለት የሚከቱበት ፖስታ ላይ የሎት ቁጥሩንና ኦርጅልና ኮፒ በመጻፍ ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 • ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደራችሁበት ሎት 1.2.8.9.10 ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን ቴከኒክ በሚለው ፖስታ ሲፒኦ ና የዋጋ ዝርዝር ሳይጨመርበት ሌሎች ተፈላጊ ማስረጃ መቅረብ ሲኖርበት ለሚወዳደሩ ቀጥተኛ ባለሙያና ብቃታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም በመስክ ጉብኝት ጊዜ የሚመለከታቸው ተባባሪ በመሆን ገለፃ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ 
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት የመጨረሻ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ወይም ዛጉዌ ህንፃ አጠገብ የሚገኘው የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የመከፈቻው ቀን ብሔራዊ በዓልና ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል ፡፡ 
 • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ከቫት ጋር አጠቃለው መፃፍ ይጠበቅባቸዋል። ቫትን አጠቃሎ ያለ መፃፍ ቫት እንዳለው ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ እንዲሁም የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ፅሁፍ የጨረታው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 • አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸው ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ለግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ያቀርባል፡፡ 
 • መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • ማስታወሻ፡- በጨረታው ተካፋይ ከሆኑ ተፈላጊ ሰነዶች ፖስታ ውስጥ ከመከተትዎ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመጀመሪያው ገፅ ላይ የሚገኘውን ማስታወሻ በትኩረት ይመልከቱ፡፡ ወይም ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥና አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ በአካል ቀርበው መረጃ ማግኘት ይችላሉ በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0118 278446 ደውለው መረዳትይችላሉ። 
 • አድራሻ፡- የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ወይም ዛጉዌ ህንፃ አጠገብ የሚገኘው የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ፡፡ 

የልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት 

የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠ/ አገልግሱት ደጋፊ የስራ ሂደት