3ኛ ዙር የደረቅ ጭነት ማመላለሻ
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2013
ሊቻ የሀድያ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ለ2013/14 ም/ዘመን የሚሆን የአፈር ማዳበሪያ በሀድያ ዞን ባሉት ወረዳዎች ለሚገኙት አ/አደሮች በሆሳዕና እና በናዝሬት ከሚገኙ መዕከላዊ መጋዘኖች ለበልግና መኸር የአፈር መዳበሪያ ምጥንና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአንድ ኪ/ሜትር ተሰልተው አማካይ ዋጋ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚህ መሠረት፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፣የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃድ ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ከሆነ ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ መልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የምችል፣
- የጨረታ ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንድያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና የሚሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ማሳያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ብዛት ቢያንስ በቀን 2000/ሁለት ሺህ / ኩ/ል ማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን ሰሌዳ ቁጥር ፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግሥታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 1000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከሊቻ የሀድያ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ኅ/የተ.ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት አምስት ተከታታይ ሥራ ቀናት በ5ኛ ቀን ከቀኑ 11፡30 /አስራ አንድ ሰዓት ተኩል/ ታሽጎ በ6ኛ ቀን 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተወዳዳሪዎቹ ወይም ህጋዊ ተወካዮቹ በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 5ኛ ወይም 6ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይዘጋል ወይም ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ሆሳዕና ከተማ ሆሳዕና ፖሊ ቴ/ሙ/ኮሌጅ በሚወስደው መንገድ ዩናይትድ ቪዥን አካዳሚ ት/ቤት ጎን
ስልክ ቁጥር፡– 0465553280/0913663320/0911539989/091670 9972
ሊቻ የሀድያ አርሶ አደሮች ኃ/የተወሰነ ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒያን