የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2013
ሊቻ የሀድያ አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበራት ኃ/የተ/ዩኒየን ለ2013/14 ም/ዘመን የሚሆን የአፈር ማዳበሪያ ሀድያ ዞን ባሉት ወረዳዎች ለሚገኙት አ/አደሮች በሆሳዕና ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለብልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ ምጥንና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአንድ ኪ/ሜትር ተሰልተው አማካይ ዋጋ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃድ ያሳደሰ፣ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ከሆነ ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ መልካም ሥራ አፈጻጻም ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና የሚሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ 200,000 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የተሸከርካሪዎች ብዛት ቢያንስ በቀን 2000 /ሁለት ሺህ ኩ/ል ማንሳት የሚችል መኪናዎችን ሰሌዳ ቁጥር ፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግሥታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምረው የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከሊቻ የሀድያ አ/አደሮች ኃ.የተ. ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምረው ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡30 /አስራ አንድ ሰዓት ተኩል/ ታሽጎ በ10ኛ ቀን 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎቹ ወይም ህጋዊ ተወካዮቹ በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛ ወይም 10ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይዘጋል ወይም ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- ሆሳዕና ከተማ ጎንቦራ ታክሲ ማዞሪያ ዋቸሞ መሠናዶ ት/ቤት በስተጀርባ
- ስልክ 0465553280/0913258568/0911539989/0916709972
ሊቻ የሀድያ አርሶ አደሮች ኃ/የተ. ህብረት ሥራ
ማህበራት ዩኒያን
ሆሳዕና