ማስታወቂያ
ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ በኣዲስ ኣበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የአርበኞች መንገድ ኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ለግለሰብ ኦፕሬተር | ወኪል/ አወዳድሮ ለተወሰነ ጊዜ መስጠት ይፈልጋል ::
ለመወዳደር ፍላጐት ያላቸው ግለሰቦች ቢያንስ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሙሉ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ::
- የትምህርት ደረጃ፣ ቢያንስ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ (ች)፣
- የነዳጅ ማደያው የሚያስፈልገውን የሥራ ማስኬጃ ካፒታል በግል የማቅረብ አቅም ያለው(ያላት)፣
- የሌላ ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ ባለቤት ወይንም ኦፕሬተር / ወኪል /ያልሆነ (ች)፣
- የነዳጅ ማደያውን ሥራ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመምራት ግንዛቤ ያለው (ያላት)፣
- . በቀን ቢያንስ የ 8 ሰዓት ጊዜ ለማደያው መስጠት የሚችል (የምትችል) ።
ከላይ የተጠቀሱን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች ብቻ ለመወዳደር ያላቸውን ፍላጐት በፅሁፍ እስከ ነሃሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ለኩባንያው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ከማመልከቻ ሰነድዎ ጋር መያያዝ ያለባቸው መረጃዎች፤
- የ2012 ዓ.ም. የተንቀሳቃሽ ወይም የቁጠባ ሒሳብዎን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቢያንስ የ 2 አመት ባንክ እስቴትመንት፣
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ፎቶ ኮፒ ፣
- የትምህርት ደረጃ የሚያሳይ የትምህርት መረጃ ፎቶ ኮፒ፣
- ላለዎት የሥራ ልምድ ማስረጃ ሊሆን የሚችል መረጃ ፎቶ ኮፒ፡፡
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ይህን ውድድር የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :: በተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ሪቴይል ክፍል በ011-4-404040 ይደውሉ።