ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ ሉማሜ ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለተማሪዎች ማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀትና ከውስጥ ገቢ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የግብርና ዕቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃዎችን
- ኮምፒዩተርና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ጫማ
- የልብስ ስፌት ማቴሪያል
- የህንፃ መሣሪያ/ኮንስትራክሽን/
- የተዘጋጁ ልብሶች
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
- የጨረታ ተሳታፊዎች የሚሞሉት ዋጋ 200,000.00 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት /VAT/ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ኮምፒዩተርና ተዛማጅ ዕቃዎች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎችና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 1.የግብርና ዕቃዎች 15.00 /አስራ አምስት ብር/ የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃዎች /30.00 ሰላሳ ብር 3. ኮምፒዩተርና ተዛማጅ ዕቃዎች 50.00/ አምሳ ብር /4.ጫማ 20.00 /ሃያ ብር 5. የልብስ ስፌት ማቴሪያል 30.00/ስሳሳ ብር / 6.ህንፃ መሣሪያ/ኮንስትራከሽን/ ብር 20.00 /ሀያ ብር 7. የተዘጋጁ ልብሶች ብር 30.00/ሰላሳ ብር/ የማይመለስ ብር በመከፈል ቢሮ ቁጥር 04 እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ ወይም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች እና ዋና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ በግ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡– 0587720704 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨምር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የዕቃውን ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ነው፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
- አሸናፊው ዕቃውን አዋ/ወ/ሉ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል ::
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው።
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን አዋበል ወረዳ ሉማሜ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ