ጄኔሬተር ግዢ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር NCB/OEB/
GOV/02/2013
ለኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሳር ቤት ለሚገኘው ዋና ቢሮ 250 KVA 200 KW 3 Phase Canopy Type ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ገዝቶ በተጠቀሰው ቦታ ማስተከል ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ጥራት ያለውን ጄኔሬተር የማቅረብ ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሙሉ መረጃውን Specification” ከሳር ቤት ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 100( አንድ መቶ) በመክፈል እንድትወስዱ እየገለፅን ዕቃውን ሳር ቤት ስሚገኘው በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ግቢ ማድረስ የምትችሉ ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ጋር፡-
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ (Clearance)፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና “Specification” ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀናት ውስጥ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ሃምሣ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ እና በኦሮሚያ ት/ቢሮ ስም የተዘጋጀ CPO ወይንም ባንክ ጋራንት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውንና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ይህንን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀናት ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡የዶክመንት ማስገቢያው ሣጥን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
- የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ፤ በማቀጥለው የመንግስት የሥራ ቀን በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ወይንም አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 0113 69 0189
ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ