የጨረታ ማስታወቂያ
በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም
- የተለያዩ ዓይነት ብረቶች (RHS፣ LTZ፤ FLAT IRON፤ ANGLE IRON፤ UCHANAL REIN FORCE BAR፣SHEET METAL)፤ የግንባታ (EAGA CLEAR GLASE፤ CEMENT)፤
- የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች፡
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታው ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ፋይናንስ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን አራት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአራት ሰዓት ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡10 ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡–ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ
ከአይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0115-52-22-55 ደውለው ቢጠይቁን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን
የህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን
ግንባታ ኢንዱስትሪ