የጨረታ ማስታወቂያ
(የግዥ መለያ ቁጥር ፍራሽ፣ ተራስ እና ቺፕውድ/uዩ/ በግጨ/21/01/2013BY) ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፍራሽ፣ ትራስ እና ቺፕውድ ለመግዛት እንዲያስችለው ኣቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መምረጥ ይፈልጋል::
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጠና በመንግሥት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፈዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድህረ ገጽ /website/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(ቢድ ቦንድ) ለምድብ 1 ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ) እና ለምድብ 2 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ) (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በካሽ የጨረታው ሳጥን እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ ማቅረብና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ከፍት ቦታ ውስጥ ሰመሙላት አስፈላጊ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር አሟልተው ኦርጂናልና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ አድርገው ፣ እሽገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በ11:00 ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፤ ሆኖም ዕለቱ( 15ኛው ቀን) በአል ወይም የዕረፍት ቀናት ከሆነ ግን በቀጥታ ተከታይ የሥራ ቀን ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በግልጽ የሚከፈተው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ግን በሚቀጥለው ተከታይ የሥራ ቀን ጠዋት 3:30 ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ቀን ዘጠና ቀናት ነው::
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዢና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡- 046 221 26 47 ፋክስ፡-(046)220 51 63
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመሣ.ቁ.5 ሃዋሳ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ