የጨረታ ማስታወቂያ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙሉ የመኪና ጥገና ስራ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ እለት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ሀዋሳ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአስራ አምስተኛው የስራ ቀን ሆኖ እለቱ ቅዳሜና እሁድ /በዓል ከሆነ በሚቀጥለው 8፡20 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በዚሁ ቀን 8፡30 በኮሌጁ ህንፃ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርቡ ተጫራቾች አገልግሎቱ ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 0462120120
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ