ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የኦዲት ጨረታ
ሀሼባን ትሬዲንግ አ.ማ በኢትዮጵያ የተመዘገበ እና ህጋዊ የንግድ ተቋም ሲሆን ድርጅታችን ከ2012-2014 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ዓመት የማህበሩን ዓመታዊ ህሳቦችን ኦዲት የሚያደርጉ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
- ከኣካውንቲግና ኦዲት ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- በIFRS ተግባራዊ ማድረግ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ቲን ነምበር ያለው።
- የመልካም አፈጻጸም ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ይውላል፡፡
- በ8ተኛው ቀን ተጫራቾች ዶከመንቶቻቸውን ስርዝ ድልዝ የሌለውን በማህበሩ ዋና መ/ቤት ጎፋ ካምፕ መሠረት ህንጻ ቢሮ ቁጥር 405 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ገቢ ያደርጋሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0912322206/ 0910441229/ 0913167832 መደወል ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-1 ስምንተኛ ቀን እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን ገቢ ያደርጋሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የአንድ አመት ሆኖ ለሦስቱም ዓመት ያገለግላል፡፡
ሀሼባን ትሬዲንግ አ.ማ