ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ…አውቶሞቢል አ.አ-02-93593 ፣ አውቶሞቢል አ.አ-02-82327

የጨረታ ማስታወቂያ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በብድር በዋስትነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ተሸከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማማሳሰቢያ

1.      ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይችላል፡፡

2.      ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ) ለጨረታው ማስከበሪያ በመክፈል መጫረት ይችላል፡፡ ተሸናፊውም ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡

3.      የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ ዋናው ቢሮ በተቋሙ ግቢ በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል::

4.      የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ገንዘብ ጨረታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ቀሪውን ክፍያ አጠናቆ ከፍሎ ተሽከርካሪውን ባይረከብ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡

5.      ከንብረቶቹ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል፡፡

6.      ንብረቱ በገዢ ስም እንዲዞር ተቋሙ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡

7.      ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

1.      አድራሻ፡- ከሃያ ሁለት ወደ መገኛኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

ስልክ ቁጥሮች 011-6623393 / 011-6630294 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡