የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ መና ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት በ2012 በጀት በሥሩ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች
- ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ስቴሽነሪ፤
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- ፈርኒቸር፤ እና
- የደንብ ልብስ፣
- የመኪና ጎማ አቅራቢ ድርጅት ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈለበትን፣ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበት የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ጨረታ ዓይነት 10,000 (አስር ሺ) ብር በወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሥም በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ በመንግስት የግዥ መመሪያ መሠረት ይበረታታሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈታው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው በስራ ሰዓት፤ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር መፈራራም አለበት፡፡
- አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ያሸነፉትን ዕቃዎች ሰራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና በራሱ ወጭ መገጣጠም የሚችል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡– 0916636698 / 0910121267
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን
ሀምበሳ ዋመና ገ/ኢ/ትብብር/ጽ/ቤት